እንዴት ማመልከት እንደሚቻል
ከማመልከትዎ በፊት የሚከተሉትን ማድረግ አለብዎት፡
- የሚፈለገውን የማንነት እና የነዋሪነት ሰነድዎን ይሰብስቡ። የጸደቁትን ቁሳቁሶች ዝርዝር በ https://seattlerelief.com/#required-documents ላይ መገምገም ይችላሉ
- አማካይ ወርሃዊ ገቢዎን ያስሉ።
ለማመልከት፣ የሚከተሉትን ማድረግ አለብዎት:
- በዚህ ድህረገጽ ላይ “Apply Now ” የሚለውን ቁልፍ ጠቅ ያድርጉ፣ ይህ ወደ ማመልከቻው ገጽ ይወስደዎታል።
- የስኮላር ፈንድ ሂሳብ ይፍጠሩ። የኢሜይል አድራሻዎን ወይም የስልክ ቁጥርዎን ብቻ መስጠት እና የይለፍ ቃል ማዘጋጀት ያስፈልግዎታል።
- ሁሉንም የማመልከቻውን ጥያቄዎች ያጠናቅቁ። በማንኛውም ጊዜ ማመልከቻዎን ማስቀመጥ (save) እና ምንጊዜም መመለስ ይችላሉ።
- አንዴ ማመልከቻዎን ከጨረሱ በኋላ፣ ማረጋገጫ የጽሑፍ መልእክት እና የማስረከቢያ መታወቂያዎን በኢሜይል ይቀበላሉ። የማመልከቻዎን አቋም ሁኔታ ለመፈተሽ ይህንን ያስቀምጡ ወይም ከድጋፍ ቡድናችን ድጋፍ ከፈለጉ።
ማመልከቻ ካስገቡ በኋላ፣ ማድረግ ያለብዎት: ለማረጋገጫዎ የኢሜይል ገቢ መልእክት ሳጥንዎን (inbox) ወይም አላስፈላጊ የኢሜይል አቃፊዎን ያረጋግጡ። እንዲሁም ማመልከቻዎን በሚያስገቡበት ቀን የጽሑፍ መልእክት ማረጋገጫ ያገኛሉ። ወደ ሲያትል የማቃለያ እርዳታ ፈንድ ሂሳብዎ ተመልሰው በመግባት እና ማመልከቻዎ እየተገመገመ መሆኑን እና የገንዘብ ሽልማት የተሰጠዎ መሆኑን ለማረጋገጥ ይችላሉ። እባክዎን ማመልከቻዎን አንድ ጊዜ ብቻ ያስገቡ።
ማመልከቻውን ለመሙላት እርዳታ ከፈለጉ እባክዎን ከአንድ የማህበረሰብ አጋሮቻችን ጋር ለመገናኘት seattlerelief.com/#app-assistance ን ይጎብኙ።
ማመልከቻዎ ከገባ በኋላ ማዘመን ወይም ማረም ከፈለጉ እባክዎን እስከ ህዳር 15 ቀን ከሌሊቱ 11:59 የፓሲፊክ መደበኛ ጊዜ (PST) አዲስ ማመልከቻ ከተሻሻለው መረጃ ጋር ያስገቡ።
የገቢ ብቁነት ገበታ